Fana: At a Speed of Life!

ለ122 ሀገራት የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለ122 ሀገራት የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት እየሰጠች መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ።

የመዳረሻ ቪዛ አንድ ዜጋ በመዳረሻ ሀገር ለሚኖረው አጭር ቆይታ የሚያገኘው ሲሆን፤ ቪዛውን ለማግኘት የሚያስፈልጉትን ጉዳዮች በአንድ ቦታ የሚጨርስበት ነው።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፤ ከዚህ ቀደም ከውጭ ሀገራት ለሚመጡ ዜጎች የቱሪስት ቪዛ አገልግሎት በኦንላይን ሥርዓት የሚሰጡበት አሠራር መዘርጋቱን ገልጸዋል።

ይሁንና የአገልግሎት መስጫ ሥርዓቱ ረዥም ጊዜ የሚወስድና ደንበኞች ቅሬታዎች በማቅረባቸው ሥርዓቱን የማስተካከል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የቱሪስት ቪዛ አሠራር እስኪስተካከል የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎቱን ተደራሽ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ122 ሀገራት የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል።

አገልግሎቱ ከዚህ ቀደም የነበረውን መጨናነቅና የተንዛዛ አሠራር ማስቀረቱንና ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን አመልክተዋል።

የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎቱ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም እድገት አስተዋጽዖ እያደረገ እንደሚገኝም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የመዳረሻ ቪዛ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማስፋት በተደረገው ጥረት አገልግሎቱ መሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.