Fana: At a Speed of Life!

በአደም ፋራህ የተመራ ልዑክ በሻንጋይ ከተማ የኮሙኒስት ፓርቲ ሙዚዬምን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ በቻይና ሻንጋይ ከተማ የኮሙኒስት ፓርቲ ሙዚዬምን ጎብኝቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በጉብኝታቸው በቻይና ፋጣን ኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበውን የኮሙኒስት ፓርቲ ታሪካዊ አመጣጥ፣ እድገት፣ የነበሩ ተግዳሮቶችና ስኬቶችን ተመልክተዋል፡፡

ከኮሙኒስት ፓርቲም በኢትዮጵያ የዜጎችን ጠንካራ የሥራ ባህል በማዳበር ሁሉም ዜጋ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የራሱን ሚና እንዲጫወት ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተሞክሮ መወሱዱ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ልዑካኑ የሻንጋይ ያንግሻን ወደብን ተዘዋውረው መመልከታቸውን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.