Fana: At a Speed of Life!

የደሴ ከተማ አሥተዳደር የነዋሪውን ጥያቄ ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ነዋሪዎች የሚያነሱትን ጥያቄ ለመመለስ አመራሩ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ የደሴ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

ከ20 ሺህ በላይ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉባቸው ሕዝባዊ ውይይቶች በ114 መድረኮች ተካሂደዋል፡፡

በመድረኮቹም በአካባቢው ካለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የኑሮ ውድነቱ ኅብረተሰቡን እያማረረ መሆኑ ተነስቷል፡፡

በመሆኑም ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባና የሕግ ማስከበር ሥራውም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የውይይቹ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡

የከተማዋን ሠላም በዘላቂነት ለማስቀጠልም አመራሩ በቁርጠኝነት ከነዋሪው ጋር በቅንጅት እንዲሠራ ጠይቀዋል፡፡

የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው ÷ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ አመራሩ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል፡፡

የተፈጠረውን አንፃራዊ ሠላም በመጠቀምም የኑሮ ውድነቱን ለመግታት እንሠራለን ብለዋል፡፡

በሰብለ አክሊሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.