Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን ወደ 43 በመቶ ማድረስ መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አምስት ዓመታት የሶማሌ ክልልን የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ከነበረበት 19 በመቶ ወደ 43 በመቶ ማድረስ እንደተቻለ የክልሉ ውሀ ቢሮ ገለጸ።

የሶማሌ ክልል ውሀ ቢሮ የመጠጥ ውሃ ዳይሬክተር አብዲ ከድር እንደገለጹት÷እንደ ክልል ያለውን የንፁህ መጠት ውሀ ፍላጎት ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ነው።

ከዚህ በፊት ከነበረው የ19 በመቶ ሽፋን አሁን ላይ ወደ 43 በመቶ ማሳደግ መቻሉንም ተናግረዋል።

የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ውሃ የማጎልበት ስራ በገጠርም ሆነ በከተማ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰው፥ በተለይም ከለውጡ ወዲህ በዘርፉ አበረታች ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

በዚህም በገጠር 29 በከተማ ደግሞ 13 የንፁህ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ነው ያሉት።

በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግንባታው የተጠናቀቀው የጅግጅጋ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትም 10 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ በቀን የሚያመነጭ ሲሆን÷ አሁን ላይ በሙከራ ሂደት ላይ ይገኛል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራው ሲገባ በከተማዋ ያለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ለ426 ሺህ ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በወንድሙ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.