የኦሮሚያ ከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት ለ704 ከተሞች ፕላን ማዘጋጀቱን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት ለ704 ከተሞች ፕላን አዘጋጅቶ ማውጣቱን አስታውቋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታረቀኝ አብዱልጀባር÷ የክልሉን ከተሞች በዘመናዊ መንገድ ለማልማት ኢንስቲትዩቱ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ይህንንም ለማሳካት በክልሉ ባሉ ከተሞች ላይ ጥናትና ምርምሮችን እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በምስራቅ ኦሮሚያ ከተሞች ያካሄደውን የምርምር ውጤት የምስራቅ ሀረርጌ ዞን እና የማያ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት ዛሬ አቅርቧል።
በመድረኩ በምስራቅ ኦሮሚያ ውጤታማ የከተሞች የፕላን ዕቅድ አጠቃቀም ለኢኮኖሚው እድገት ያለው አስተዋጽኦ ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
በኢዮናዳብ አንዱዓለም