Fana: At a Speed of Life!

ኢንስቲትዩቱ የአፍሪካ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የልሕቀት ማዕከል እንዲሆን የቀረበው ምክረ ሃሳብ ተቀባይነት አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የልሕቀት ማዕከል እንዲሆን የቀረበው ምክረ ሃሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿ።

የአፍሪካ የአይሲቲ እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ በአፍሪካ ህብረት የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው ኢትዮጵያን በመወከል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኤሌክትሮኒክ መንግስት ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አብዮት ሲናሞ(ዶ/ር ኢ/ር) እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በስብሰባው የኢትዮጵያው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት “የአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የልሕቀት ማዕከል” እንዲሆን በኢትዮጵያ በኩል ጥያቄው ቀርቦ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

በዚህም በአፍሪካ ሀገራት የአይሲቲና የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴሪያል አባላት ተቀባይነት ማግኘቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.