በመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች የጋራ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
ውይይቱ በ2015 በጀት ዓመት በተገኙ አበረታች ውጤቶች፣ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በከተማ አስተዳደሩ በተሰሩ ስራዎች እንዲሁም የተያዘው በጀት ዓመት የከተማዋ የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡
በጋራ ህዝባዊ የውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች መገኘታቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡