ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡
ግንባታው በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ነው እየተገነባ የሚገኘው፡፡
የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግብዓቱን የማብላላት ተግባር ያለውን የፋብሪካው ክፍል እና ወደ ቀጣዩ ሂደት ማስተላለፊያ ቱቦ መጠናቀቁም ተገልጿል፡፡
ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ ከቻይና ባለሀብቶች ጋር በመሆን እየተገነባ ያለውን ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ቀንና ማታ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ሂደትን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡
በአዲሱ ሙሉነህ