Fana: At a Speed of Life!

የወንጀል መከላከልና የምርመራ ሥራዎች በላቀ ሙያዊ ብቃት እየተከናወኑ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወንጀል መከላከልና የምርመራ ሥራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በላቀ ሙያዊ ብቃት እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የፖሊስ የመጀመሪያ ሥራ መረጃ መር የኅብረተሰብ አገልግሎት ላይ የተመሰረተ የወንጀል መከላከል ተግባር በመሆኑ በዚሁ መሰረት እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ አስታውቀዋል፡፡

ፌዴራል ፖሊስ በዜጎች እና በሀገር ላይ የሚቃጡ ወንጀሎችን በመከላከልና የምርመራ ሥራዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በላቀ ሙያዊ ብቃት እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

ይሄው አሠራርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

የዜጎችን ደኅንነት በአስተማማኝ መልኩ በመጠበቅ እየተደረገ ባለው ጥረትም የኅብረተሰቡ ተሳተፎ የላቀ ሚና እንዳለው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሀገሪቱን ብሎም የቀጣናውን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥም ከኢንተርፖል እንዲሁም ጎረቤት ሀገራት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.