Fana: At a Speed of Life!

የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ በዓል በድምቀት ይከበራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ በዓል በነገው ዕለት በድምቀት ይከበራል።

ዓመታዊ ክብረ በዓሉ መስከረም 21 በዞኑ አምባሰል ወረዳ ግሸን ተራራ ላይ በደመቀ መልኩ የሚከበር ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች እና ጎብኚዎች ወደ ቦታው እየገቡ ነው።

በዓሉ እንደወትሮው ሁሉ ዘንድሮም በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር አስታውቋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ የኖረ የእንግዳ ተቀባይነቱን ለማሳየት የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሚመራቸው የተለያዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ስራ ገብተዋል።

በዋናነት በዓሉ በሰላም እንዲከበር የጸጥታ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሲሰራ የቆየ ሲሆን የመከላከያ ሰራዊትና የክልሉ የጸጥታ ተቋማት በጋራ በመሆን ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ።

በሙሉቀን አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.