Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት “ቅኝት” የተሰኘ ትምህርታዊ ገለጻን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመጀመሪያውን “ቅኝት” የተሰኘ ትምህርታዊ ገለጻን ጅማሬ ዛሬ አብስሯል፡፡

በመድረኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑት የልማት ምጣኔ ሃብት ጄፈሪ ሳክስ (ፕ/ር) በተከፋፈለው አለም ዘላቂ ልማትን በገንዘብ በመደገፍ ላይ ያሉ ተግዳሮቶች እና መፃዒ ዕድሎች ላይ ንግግር ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢኮኖሚ ምሁሩ ጄፈሪ ሳክስ (ፕ/ር) ህዝብን ተደራሽ የሚያደርጉ የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ስራዎች ለአገራት ፈጣን እድገት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

ቻይና ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበችው ፈጣን እድገት በዚህ ረገድ ተጠቃሽ መሆኑንም አንስተዋል።

በተለይ በትምህርት ተደራሽነትና በመሰረተ ልማት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የአገራትን መጻኢ ለውጥ በመወሰን ረገድ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችው ተግባር የሀገሪቷን ፈጣን እድገት የሚያስቀጥል ኢንቨስትመንት መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ያላትን የታሪክና የባህል አቅም ለቱሪዝም ማዋል ላይ በስፋት ሊሰራ ይገባልና በቀጣናው ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ትብብር የልማት አቅም አድርጎ መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.