ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለኬንያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለኬንያውያን 60ኛ አመት የነጻነት ቀን በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ በ60ኛው የኬንያ ነጻነት ቀን ላይ በኬንያ ናይሮቢ ተገኝተው በኢትዮጵያ ህዝብ ስም መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸው÷ ለኬንያውያን ያላቸውን ክብር ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያውያንን ወክለው መገኘታቸውን ገልጸው “እንኳን ለነጻነት ቀን በዓል ሁላችሁም አደረሳችሁ” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ለኬንያውያን ስኬት ፣ ብልጽግና እና ደስታ መልካም ምኞታቸውንም በመድረኩ ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በ60ኛው የኬንያ ነጻነት ቀን (ጃምሁሪ) በዓል ላይ ለመታደም ትናንት ወደ ናይሮቢ ማቅናታቸው ይታወቃል፡፡