Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ የፓስፖርት ቴክኖሎጂ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል የተባለ ሥምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ የፓስፖርት ቴክኖሎጂ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን አመላካች የተባለለት ሥምምነት በዛሬው ዕለት በተለያዩ ተቋት መካከል ተፈርሟል፡፡

የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት፣ ቶፓን ግራቪቲ ኢትዮጵያ አክስዮን ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እና የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት የፓስፖርት አቅርቦትና አገልግሎት ሥራን በኢትዮጵያ ለመጀመር የሚያስችላቸውን ስምምነትን ተፈራርመዋል።

ሥምምነቱ የኢትዮጵያን የፓስፖርት አሠራር በማዘመን፣ አዲስ ለተነደፈው የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት የተሻሻሉ የደኅንነት ባሕሪያትን እና የተሻሻለ ቅልጥፍናን በማምጣት ረገድ ትልቅ ፋይዳ አለው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ለኢትዮጵያ የፓስፖርት ቴክኖሎጂ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን የሚያመላክት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ወደ ተሻለ የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደት እንከን የለሽ ሽግግር ለማድረግ ቃል መገባቱን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡

ፓስፖርት ማተሚያ ፋብሪካው በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ እንደሚሆንም ተጠቅሷል፡፡

ይህ ፈር ቀዳጅ የተባለለት ሥምምነት በማንነት፣ በሰላማዊ ጉዞ እና በደኅንነት ዙሪያ ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል ነው የተባለው።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.