Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የስደተኞችንና የተቀባይ ማህበረሰቡን ህይወት ለማሻሻል መስራቷን ትቀጥላለች – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የስደተኞችን ህይወት ለመለወጥ ከአጋር አካላት ጋር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ መንግስት እና በአይኬ ኢ ኤ ፋውንዴሽን ትብብር የመልካዲዳ የስደተኛ ቃል ኪዳንና እና የቀብሪ በያህ ፍኖተ ካርታ የተሰኙ የስደተኞችን ህይወት ለማሻሻል የተዘጋጁ ሰነዶች በዛሬው ዕለት በጄኔቫ ይፋ በተደረጉበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው።

የአይ ኬኢኤ ፋውንዴሽን ሰነዶች እንዲዘጋጁ ድጋፍ በማድረጉ አቶ ደመቀ ምስጋና ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ለስደተኞች ከለላ በመስጠት እና ከተቀባይ ማህበረሰብ ጋር እንዲቀላቀሉ በማድረግ ሒደት የግሉ ዘርፍ አጋርነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ምክንያት በሀገራቸው መኖር ያልቻሉ በርካታ ስደተኞችን በመቀበል ቀዳሚ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ናት፡፡

የውጭ ስደተኞችን በአግባቡ ለማስተናገድ የሚያስችል ፖሊሲ ቀርፃ በመተግበር ላይ እደምትገኝም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.