ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ 88ኛውን የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል ቀን ለማክበር ቢሾፍቱ ተገኝተዋል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ 88ኛውን የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል ቀን ለማክበር በቢሾፍቱ ከተማ ተገኝተዋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ቢሾፍቱ በሚገኘው የዓየር ኃይል መኮንኖች ክበብ ሲደርሱ ወታደራዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ ሙሉ እድሳት የተደረገለትን የዓየር ኃይል መኮንኖች ክበብ መርቀው ከፍተዋል።
የዓየር ኃይል መኮንኖች ክበብ በ1955 ዓ.ም የተገነባ ሲሆን÷ መዝናኛ ክበቡ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እድሳት ተደርጎለት ሠራዊቱን እና ቤተሠቡን እንዲሁም የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
88ኛው የዓየር ኃይል የምስረታ በዓል በዛሬው ዕለት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ጀኔራል መኮንኖች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በፓናል መከበር ይጀምራል፡፡