Fana: At a Speed of Life!

የሐይማኖት ተቋማት ሰላምን ለማደፍረስ የሚሠሩ አካላትን በንቃት መከላከል እንደሚጠበቅባቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐይማኖት ተቋማት አንድነትና መከባበርን ከማስተማር ጎን ለጎን ሰላምን ለማደፍረስ የሚሠሩ አካላትን በንቃት ሊከላከሉ እንደሚገባ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከደበ አስገነዘቡ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ምስረታ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር÷ የሐይማኖት ተቋማት የሕዝቦችን ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከር ተምሳሌታዊ ተግባር ሊፈጽሙ ይገባል ብለዋል፡፡

አንድነትና መከባበርን ከማስተማር ጎን ለጎንም ሰላምን ለማደፍረስ የሚሠሩ አካላትን በንቃት ሊከላከሉ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይም በአንድነት መሥራት ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዋና ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው÷ የሐይማኖት ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት ከተወጡ ሀገራችን የሰላም እጦት ስጋት አይሆንባትም ብለዋል፡፡

በዚህም ዘርና መሰል ሁኔታዎችን መነሻ የሚያደርጉ ልዩነቶችን ከማጥበብና ከማስወገድ አንጻር የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ አስታውቀዋል፡፡

ለሀገር ሰላምና ልማት መረጋገጥም በየተሰማራንበት አስተምኅሮ ትውልድን ማነጽ አለብን ብለዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.