Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ፈይሰል አልይ ከየመኑ አቻቸው አምባሳደር ራጅህ ሁሴን ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በየመን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፈይሰል አልይ ከየመኑ አቻቸው አምባሳደር ራጅህ ሁሴን ባዲ ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየና ታሪካዊ ግንኙነት በማጠናከር የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

አምባሳደር ፈይሰል የመንና ኢትዮጵያ የቆየ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ጠቅሰው ÷ የየመን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱም ነው የጠየቁት፡፡

መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ለሚፈልጉ ባለሃብቶችም ምቹ ሁኔታ እንዳለ መግለጻቸውን በዶሃ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጠር የየመን አምባሳደር በበኩላቸው ÷ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት የበለጠ ለማጠናከር ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም ነው የተናገሩት፡፡

በሁለቱ ሀገራት ያለውን የህዝብ ለህዝብ ታሪካዊ ትሥሥር መሠረት በማድረግ የመንና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነትን እና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማሳደግ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡

እንዲሁም አምባሳደር ፈይሰል አልይ ከቀጠር የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጃስም ቢን ራሽድ አልቡዓይኔን ጋርም ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም እንዳሉት ፥ ሁለቱ ሀገራት ያላቸው ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያሳድግ መልኩ ወደ ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ከፍ ማድረግ ይገባል፡፡

እንዲሁም የሀገራቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖችም በትምህርት፣ በስፖርት ልማት ዘርፍ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸው ሁኔታ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተስማምተዋል ነው የተባለው፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.