Fana: At a Speed of Life!

በተጠናቀቀው 6 ወር 57 ሺህ ይዞታዎች ተመዘገቡ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው የበጀት ዓመት በተጀመረው የ7ኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ሂደት 57 ሺህ ይዞታዎችን መመዝገብ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታና ምዝገባ መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ግፋወሰን ደሲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በ10 ክፍለ ከተሞች የ6ኛ እና 7ኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

በ7ኛ ዙር የይዞታ ማረጋገጥና የምዝገባ ስራም በተያዘው የበጀት ዓመት በ10 ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 85 ቀጠናዎች 383 ሰፈሮች የመደዳ የቁራሽ መሬት ይዞታ የማረጋገጥና ምዝገባ ሥራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዘንድሮ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም 80 ሺህ የኮንዶሚኒየምና የአፓርታማ ይዞታ የማረጋገጥ ምዝገባ እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.