Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቀነስ ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ እና የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ እንዲሁም ለወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ የሥራ ሀላፊዎች በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተተከሉ ችግኞች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው በመመልከት እንክብካቤ አድርገዋል።

በዚህ ወቅት አቶ ኦርዲን እንዳሉት÷ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም የኢትዮጵያን የልማት ራዕይ ለማሳካት ወሳኝ ነው፡፡

መርሐ ግብሩ በተለይም ለአየር ንብረት ለውጥ፣ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስና ለወጣቶች የስራ ዕድልን ከመፍጠር አኳያ ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብና ውሃ ማጠጣትም አስፈላጊ ስለመሆኑን መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ነስረዲን አሕመድ በበኩላቸው÷ የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁ የመንከባከብና ውሃ የማጠጣትና ስራ እየተሰራ መሆኑንና ተናግረዋል።

ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት ስለመፅደቃቸውም ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.