Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት አስተባባሪ አብዱረህማን አብደላ ገለጹ፡፡

የአርብቶ አደሮች ቀን በኦሮሚያ ክልል ለ19ኛ ጊዜ በአዳማ እየተከበረ ነው።

አቶ አብዱረህማን በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ ክልል በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

በተቀናጀ መልኩ የአርብቶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል በተሠራው ሥራም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ከ5 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች እንደሚገኙ ገልጸው÷ የልማት ተጠቃሚነታቸውንና ሕይወታቸውን የማሻሻል ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በአከባበሩ ላይ የክልልና የፌደራል የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአርብቶ አደሩ ማኅበረሰብና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በወንድሙ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.