ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የምስራቅ አፍሪካ የአርብቶ አደሮች ኤክስፖን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የምስራቅ አፍሪካ የአርብቶ አደሮች ኤክስፖን ጎብኝተዋል፡፡
ፕሬዘዳንቷ ከጥር 17 እስከ ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየውን የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
እንዲሁም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ኤክስፖውን ጎብኝተዋል፡፡
በተጨማሪም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ኤክስፖውን ጎብኝተዋል፡፡
ኤክስፖው ለመጀመሪያ ጊዜ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን÷”አርብቶ አደርነት፣ የምስራቅ አፍሪካ ህብረቀለም” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በዋናነት የኤክስፖው አላማ የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች የሚያጋጥማቸውንና ያለፉባቸውን መንገዶች እርስ በርስ የሚለዋወጡበትና ልምድ የሚቀምሩበት እንዲሁም የጋራ ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት ነው ተብሏል።
በዓለምሰገድ አሳዬና ማርታ ጌታቸው