በጋራ ጥረታችን የጀመርነው ሥራ ፍጥነቱን ጠብቆ እንዲሄድ እንረባረብ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና አቅማችንን በምሉዕ ለመጠቀም በጋራ ጥረታችን የጀመርነው ሥራ ፍጥነቱን ጠብቆ እንዲሄድ መረባረብ ይገበል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷የወቅቱ የመስኖ ስንዴ ውጠየት እያሳየ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በግብርናው ዘርፍ እንደ ሀገር ያለውን አቅም በሙሉ ለመጠቀም እንዲቻልም በጋራ ጥረት የተጀመሩ ሥራዎች ፍጥነታቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡