Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው ኢንተርናሽንል ዳኛ ይድነቃቸው ዘውገ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው ኢንተርናሽናል ዳኛ ይድነቃቸው ዘውገ (ቦቸራ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ይድነቃቸው ዘውገ ከተጫዋችነት እስከ ዓለምአቀፍ ዳኝነት ብሎም በኮሚሽነርነት ከሀገር አቀፍ እስከ አኅጉር አቀፍ መድረኮች አገልግሏል፡፡

በኩላሊት ህመም ምክንያት ሕክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የድሬዳዋ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በይድነቃቸው ዘውገ ሕልፈት የተሰማውን ሐዘን እየገለፀ÷ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹ እና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.