የብራዚል ቀዳማዊት እመቤት ጃንጃ ሉላ ዳ ሲልቫ የምገባ ማዕከላትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል ቀዳማዊት እመቤት ጃንጃ ሉላ ዳ ሲልቫ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን የተስፋ ብርሃን እና የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የምገባ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡
እንዲሁም በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የተገነባዉን የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን ጎብኝተዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ “በቀጣይም የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ አጠናክረን በትብብር አብረን ለመስራት የሚያስችለንን ውይይትም አድርገናል” ብለዋል::