Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የውይይት መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ባለው ውይይት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአማራ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡፡

በተመሳሳይ በየካ ክ/ከተማው መድረክ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማም የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር ደስታ ሌዳሞ እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር ) በተገኙበት ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

እንዲሁም በልደታ ክ/ከተማ እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ውይይት የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ እና የብልጽግና ፖርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

ሕዝባዊ ውይይቱ የማሕበረሰቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች በመፍታት ሀገራዊ ድሎችን ለማስቀጠል ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.