ኢትዮጵያና ኔዘርላንድስ የ10 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ የ10 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ አምባሳደር ሄንክ ያን ባከር ተፈራርመዋል።
ድጋፉ በሞጆ ደረቅ ወደብ ለሚገነባው የአትክልት እና ፍራፍሬ ማቆያ መጋዘን ግንባታ ሥራ እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡
ወ/ሮ ሰመሪታ ግንባታው በ2 ዓመት ውስጥ ተገንብቶ አንደሚጠናቀቅ ጠቁመው÷ የኔዘርላንድስ መንግስት ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
በበረከት ተካልኝ