Fana: At a Speed of Life!

ሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎችን የሚያገናኘው የዳዬ-ጭሪ-ናንሴቦ መንገድ ግንባታ 84 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎችን በቅርበት የሚያስተሳስረው የዳዬ-ጭሪ-ናንሴቦ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም 84 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

የመንገድ ግንባታው 71 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ 47 ኪሎ ሜትሩ የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል ተብሏል፡፡

ለግንባታው የሚውለው 1 ቢሊየን 723 ሚሊየን 608 ሺህ 313 ብርም በኢትዮጵያ መንግሥት መሸፈኑ ተመላክቷል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ከዳዬ ከተማ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል እየተገነባ ከሚገኘው የኤዶ-ሴሮፍታ-ወርቃ መንገድ ፕሮጀክት ጋር እንደሚገናኝ ተጠቅሷል፡፡

መንገዱ በገጠር 10 ሜትር እና በከተማ 19 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ መሆኑን ከአሥተዳደሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.