Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ከተማ ግንባታቸው ከተጀመሩ 56 ት/ቤቶች 39ኙ አገልገሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው የበጀት ዓመት ግንባታቸው ከተጀመሩ 56 ትምህርት ቤቶች 39ኙ ግንባታቸው ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የሸገር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

የአሥተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ፍራኪያ ካሣሁን እንደገለጹት÷ በያዝነው የበጀት ዓመት ግንባታቸው ከተጀመሩ 56 ትምህርት ቤቶች 39 ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡

በግንባታ ላይ የሚገኙ ቀሪ ትምህርት ቤቶችንም በዚሁ በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ከግንባታው ጎን ለጎንም የግብዓት እጥረት ላለባቸው ትምህርት ቤቶች ግብዓት የማሟላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.