Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት 13ኛ ዓመትን አስመልክቶ የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበትን 13ኛ አመት አስመልክቶ የሩጫ ውድድሮች ተደርገዋል።

ውድድሩ እየተደረገባቸው ከሚገኙ ከተሞች መካከል አሰላ፣ አዳማ ፣ ጅማ፣ ሻሸመኔ፣  ነቀምቴ፣ ማያና አምቦ ይገኙበታል።

በሩጫ ውድድሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለፍጻሜ እስኪበቃ እና በሌሎች ሀገራዊ የልማት ስራዎች በንቃት እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል።

በሸገር ከተማ አስተዳደር በተካሄደው የሩጫ ውድድር ላይ የተሳተፉት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኦሮሚያ ክልል ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በቦንድ ግዢና በስጦታ ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉ ገልጸዋል።

በገላና ተስፋ፣ በያሲን ሸምሱዲን፣ በጥላሁን ይልማ፣ በአብደላ አማን እና በወርቃፈራሁ ያለው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.