Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ምሁራን የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል አልፎ አልፎ የሚከሰተው የጸጥታ መደፍረስ በዘላቂነት እንዲፈታ ምሁራን የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ተጠየቀ።

በክልሉ የሚገኙ ምሁራን ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ የተለያዩ ከፋፋይ ትርክቶችን የሚነዙ አካላት ክልሉን የግጭት ቀጠና ለማድረግ በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው።

በፅንፈኝነት ታውረው የሰዎች ሕይወት እንዲጠፋ የሚያደርጉ አካላትን በህግ ተጠያቂ የማድረጉን ስራ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ምሁራንም በህብረተሰቡ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነትና እውቀትን በመጠቀም መንግስት በሚሰራው የሰላምና ፀጥታ ተግባር ተባባሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ምሁራን በበኩላቸው÷ ሠላም የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ የተጀመረው ሠላማዊ እንቅስቃሴ እንዲጠናከር የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

አብሮነት መልካም እድልን የሚፈጥር እንጂ ለግጭት የሚዳርግ ባለመሆኑ ሁሉም አካል ከጥላቻና ከፋፋይ አጀንዳ ራሱን ማራቅ ይጠበቅበታል ብለዋል።

በክልሉ የሚታዩትን አለመግባባቶች በውይይት በመፍታት ሰላምን ለማምጣት ከምንጊዜውም በበለጠ ጠንክረው እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.