Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በኢትዮጵያ የስራ ዘመናቸዉን የጨረሱትን የኔዘርላንድስ አምባሳደር አሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘዉዴ በኢትዮጵያ የስራ ዘመናቸዉን የጨረሱትን የኔዘርላንድስ አምባሳደር ቤንጌት ቫንን አሰናበቱ፡፡

ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት አምባሳደሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉን ግንኙነት ለማጠናከር ስላበረከቱት አስተዋጾ አመስግነዉ ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉን ግንኙነት ለማዳበር የድርሻዋን እንድምትወጣ ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሩ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ባሳለፉት አራት አመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል በንግድ እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ያለዉን ግንኙነት ለማጎልበት የተሰራዉን ስራ መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.