Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በ #ጽዱኢትዮጵያ ቴሌቶን ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ለ #ጽዱኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 50 ሚሊየን ብር ለማሳባሰብ ታስቦ እየተካሄደ በሚገኘው የዲጂታል ቴሌቶን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ያስጀመሩት የ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ለከተማችን ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡

መላው የከተማችን ነዋሪዎችም ንፅህና የዘመናዊት ምልክት ከዚያም አልፎ ክብር መሆኑን በመገንዘብ እንዲሁም ነውር የሆነውን ሜዳ ላይ መፀዳዳት ለማስቀረት በተጀመረው የዲጂታል ቴሌቶን ንቅናቄ ላይ በንቃት ተሳተፉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016፣ በስዊፍት ኮድ NBETETAA፣ በዲጂታል ባንኪንግ ከንግድ ባንክ ወደ ንግድ ባንክ በአንድ ጊዜ 100 ሺህ ብር በቀን 6 ጊዜ መላክ ይቻላል፣ ከሌላ ባንክ ወደ ንግድ ባንክ ሲላክ ደግሞ በአንድ ጊዜ 25 ሺህ ብር በቀን 4 ጊዜ መላክ ይቻላል፡፡

የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.