Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፓኪስታን በትምህርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በትምህርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ከፓኪስታን የከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙክታር አህመድ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ አምባሳደር ጀማል የኢትዮጵያ መንግስት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በትምህርት ዲፕሎማሲ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

የትምህርት ዘርፍ ትብብሩ በሀገራቱ መካከል ዘላቂ ግንኙነት እንዲፈጠር ትልቅ እገዛ እንደደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡

በፓኪስታን የከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙክታር አህመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ እና በፓኪስታን መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር የልዑካን ቡድን የልምድ ልውውጥ እንዲመቻችም  መጠየቃቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.