Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማቱ ሀገሪቱ በብልጽግና ጉዞ ላይ መሆኗን ያሳያል – የምክር ቤት አባላት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ ሀገሪቱ በብልጽግና ጉዞ ላይ መሆኗን ማሳያ ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡

አባላቱ ከፒያሳ አራት ኪሎ እና ከሜክሲኮ ሣር ቤት የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ገለጻ÷ ፕሮጀክቱ ለ47 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን፤ ሥራው 24 ሠዓት በፈረቃ በመሠራቱ ከታሰበው ጊዜ ቀድሞ መጠናቀቁን እና ይህም የወጣቱን የሥራ ባህል መቀየሩን አብራርተዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ሥራው አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ዓለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች ከተማ እንድትሆን አስችሏታል ማለታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የትራፊክ ፍሰቱ እንዲስተካከል፣ ለእግረኞች ምቾት እና ደኅንነትም ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት፡፡

ጎብኝዎቹ በበኩላቸው÷ የኮሪደር ልማት ሥራው ሀገሪቱ የብልጽግና ጉዞ ላይ መሆኗን እና መንግሥትም የጀመረውን የመጨረስ ባህሉ እያደረገ መምጣቱን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.