Fana: At a Speed of Life!

ኢራን ከኢትዮጵያ ጋር በግብርና ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር አሊ አክባር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በግብርና ኢንቨስትመንት እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የልምድ ልውውጥ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)÷ የኢራን መንግስት በግብርናው ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ያሳየውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡

ኢትዮጵያም በግብርና ቴክኖሎጂ ላይ ከኢራን እውቀት ለመቅሰም ፍላጎት እንዳላትም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ እንዳላት ጠቁመው÷ የኢራን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ማልማት እንደሚችሉ ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር አሊ አክባር በበኩላቸው፤ የኢራን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በግብርናው መስክ የልምድ ልውውጥ የማድረግና በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.