የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ተቋማዊ የአሰራር ለውጥ እንደሚደረግ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ተቋማዊ የአሰራር ለውጥ እንደሚደረግ አስታወቁ፡፡
አፈ ጉባዔው ከምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ከጽህፈት ቤት ሃላፊ እና ዳይሬክቶሬቶች ጋር አዲሱ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ በተገኙበት ትውውቅ እና በአሰራር ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም የጽህፈት ቤቱ የሶስቱ ዓላማ ፈጻሚዎች እና የሕዝብ ግንኘነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት እስካሁን የተሰሩ ዋና ዋና የስራ አፈጻጸሞች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
እንዲሁም የ2012 በጀት ዓመት እቅድ እና አፈጻጸም ላይ ውይይት መደረጉን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ መነሻነት የምክር ቤቱ ሁለንተናዊ አሰራር እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጎበት አጠቃላይ የአሰራር ማሻሻያ እንደምደረግበትም ተናግረዋል፡፡