Fana: At a Speed of Life!

የሀገራዊ መግባባት አለመኖር ለውድመትና ለውጪ ጠላቶች ሴራ ተጋላጭ ያደርጋል – ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራዊ መግባባት አለመኖር ለውድመት እና ለውጪ ጠላቶች ሴራ ተጋላጭ ያደርጋል ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

“የዜጎች ተሳትፎ ለተሳካ አካታች ሀገራዊ ምክክርና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ባለድርሻዎች በተገኙበት ሁለተኛው የፓርላማ የዜጎች ፎረም ተካሂዷል።

በፎረሙ ገለጻ ያደረጉት ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፤ ሀገራዊ አንድነት መገንባት በርካታ ውጣ ውረዶች ያሉበት፤ ጊዜ የሚወስድና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

የሀገራዊ መግባባት አለመኖር የእርስ በርስ ግጭቶችን በመፍጠር ለሃብት ውድመት፣ ኢኮኖሚያዊ ድቀትና ለውጪ ጠላቶች ሴራ ተጋላጭ እንደሚያደርግ አመላክተዋል።

ከታሪክ ስህተትና ጥፋት ለመማር ዝግጁ መሆን፣ ለትውልድ የሚሻገሩ ጉዳዮች ሌሎች ችግሮችን ሳይወልዱ መፍትሔ መስጠትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የምንማረው ነው ብለዋል።

ሀገራዊ አንድነት መገንባት የተረጋጋ ፖለቲካዊ ሥርዓት ለመገንባትና ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ አቅም ለመገንባት ያስችላል ሲሉም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ያገኘችውን ሀገራዊ ምክክር የማድረግ ዕድል ሁሉም አካላት በአግባቡ መጠቀምና በቁርጠኝነት መጠበቅ እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.