Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎ የህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም እጩ ዋና ዕምባ ጠባቂ፣ ምክትል ዕምባ ጠባቂ እና የዘርፍ እምባ ጠባቂ ሹመቶችን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

እንዲሁም የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ፣ የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ እና የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ምክር ቤቱ ያደምጣል፡፡

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.