የኢፌዴሪ የመደመር መንግሥት ተቋማት ውስጥ የተሾሙ አመራሮች ስም ዝርዝር
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሰባት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ብርሃኑ ዘውዴ – የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
2. ታምራት በየነ (ዶ/ር) – የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
3. አቶ ብርሃኑ ፈይሳ – የመንግስት ረዳት ተጠሪ
4. ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ – የመንግስት ረዳት ተጠሪ
5. ዶ/ር መሃመድ እንድሪስ – በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞህራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ረዳት አስተባባሪ
6. ወ/ሪት ፈዲላ አባብያ – በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዲጂታል ሚዲያ አስተባባሪ
7. አቶ ተስፋዬ ይገዙ – በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ረዳት አስተባባሪ ሆነው ተሹመዋል።