Fana: At a Speed of Life!

ሚድሮክ በግሉ ዘርፍ ልዩ አሻራ ያሳረፈ ድርጅት ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚድሮክ ባለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ልዩ አሻራ ያሳረፈና በሀገር ግንባታ ውስጥ የራሱን ድርሻ የተወጣ ተቋም ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሚድሮክ ለሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው አውደ ርዕይ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት÷ ሚድሮክ ሀገር በጠራችው ጊዜ ሁሉ በፍጥነት የሚደርስና ለሀገሩ የሚተጋ ተቋም ነው።

የተቋሙ የኢኮኖሚ ታሪክ ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ታሪክ ጋር የተሳሰረ መሆኑን ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚድሮክ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከቱን አመልክተዋል።

አንድ ተቋም ታላቅ የሚሆነው በሚያመርተው ምርት ወይም በሚሰጠው አገልግሎት ብቻ እንዳልሆነ በማንሳት ትርፉን ለምን እንደሚጠቀም፣ ለሀገሩ ምን ያህል እንደሚመልስ እና በሚያስፈልግበት ጊዜ ከሀገሩ ጎን መቆም መቻሉም ጭምር እንደሆኑ አስገንዝበዋል።

በዚህ ረገድ ሚድሮክ ከዓመታዊ የተጣራ ትርፉ 10 በመቶውን ለማኅበራዊ ኃላፊነት በመመደብ የንግድ ስኬትን ከሰው ሕይወት ጋር የማገናኘት ቁርጠኝነት ያሳየ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የተቋሙ ተሞክሮ ሌሎች የግሉ ዘርፍ ተቋማትም ሊከተሉት የሚገባ ምሳሌ መሆኑንም አንስተዋል።

በተጨማሪም ሚድሮክ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ ሀገሪቱን ከውጭ ምንዛሬ ጫና ለማላቀቅ በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት ውስጥ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ያለ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ድርጅት መሆኑን ጠቁመዋል።

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.