Fana: At a Speed of Life!

6 ጆንያ የባቡር ሀዲድ ተገጣጣሚ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ አስተዳደር በስድስት ጆንያ የተከዘነ የባቡር ሀዲድ ተገጣጣሚ መያዙ ተገለጸ።

የከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ መንግስቱ አረጋው እንደገለጹት÷ የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት የተቀናጀ የቤት ለቤት ፍተሻ የተዘረፈው የባቡር ሀዲድ ተገጣጣሚ ሊያዝ ችሏል።

በከተማዋ በተደረገ ሁሉን አቀፍ ድንገተኛ ፍተሻ ልዩ ስሙ መልካ ጨፌ በተባለ አካባቢ 462 የባቡር ሀዲድ ማሰሪያና ተገጣጣሚ በ6 ጆንያዎች በብርድ ልብስ ተጠቅልሎ በባዶ ቤት ውስጥ መያዙን ተናግረዋል።

የዘረፋ ድርጊት የፈጸመውን ፀረ ልማትና ፀረ ህዝብ አካል በቁጥጥር ስር ለማዋል ጉዳዩ በሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ተገቢው ክትትል እየተደረገ እንደሆነም ጠቁመው፤ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ መጠየቃቸውን የመርሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.