Fana: At a Speed of Life!

አጀንዳዎችን የማጣጣም ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስምንቱ ቡድኖች የተስማሙባቸውን ምክረ ሀሳቦች እንዲያናብብ፣ እንዲያጣጥምና እንዲያደራጅ የተቋቋመው ቡድን ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል አለ፡፡

እያንዳንዳቸው 500 አባላት ያሏቸው ስምንት ቡድኖች ያዘጋጇቸውንና የተስማሙባቸውን ምክረ ሀሳቦች በትናንትናው ዕለት ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለት ደግሞ 120 አባላት ካሉት ቡድን የተመረጡ 34 አባላት በስምንት ንኡስ ቡድኖች ተከፋፍለው የእያንዳንዱን የአጀንዳ ሃሳቦችን በጥልቀት ሲመረምሩ ውለዋል፡፡

አባላቱ በተለያዩ አጀንዳዎች ስር በተደጋጋሚ የተነሱ ሃሳቦች እንዳይኖሩ የመለየት፣ ያለ ምድባቸው የተነሱ ሃሳቦችን ወደሚመለከታቸው የአጀንዳ ምድብ የመመለስ እንዲሁም የማጥራትና የማጣጣም በመስራት ላይ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

ይህ ስራ የሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦችን ወጥ በሆነና ጥራት ባለው መልኩ ለማደራጀት የሚያግዝ ሲሆን፥ ሂደቱ እስከ ነገ የሚቀጥል መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.