ፕሬዚዳንት ታዬ ለብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች አቶ ተመስገን ጥሩነህና አቶ አደም ፋራህ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ነው የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡