Fana: At a Speed of Life!

64 ሆስፒታሎች ዲጂታል የጤና ሥርዓቱን የሚያግዙ ቁሳቁሶች ተረከቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጤና ሚኒስቴር ለዲጂታል የጤና አገልግሎት ሥርዓት ማስጀመሪያ የሚውሉ 642 ኮምፒውተሮችን በክልሎች ለሚገኙ 64 ሆስፒታሎች አስረከበ፡፡

የጤና አገልግሎት ሥርዓት ዘመኑን በሚመጥን ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶክተር አየለ ተሾመ ተናግረዋል፡፡

በተቋማት ዲጂታል የጤና አገልግሎት ሥርዓትን ለማስጀመር የመሰረተ ልማትና ተቋማቱን በቁሳቁስ የማሟላት ሥራ ትኩረት እንደተሰጠውም ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ 800 የሚደርሱ ተቋማት የጤና መረጃዎችን በዲጂታል ሥርዓት እያደራጁ እንደሆነ ገልጸው፤ የአገልግሎት ክፍያንም ወደሥርዓቱ ለማስገባት በሂደት ላይ ናቸው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት 117 የሚደርሱ የጤና ተቋማት ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

በተያዘው ዓመት በተለይ ከጤና ተቋማት ወደሌላ ጤና ተቋማት የሚደረግ ቅብብሎሽን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማድረግ ወደሥራ መገባቱንም አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.