የኢትዮ ፓኪስታን ግንኙነትን ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ ደረጃ ለማድረስ …
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ ደረጃ የማድረስ ፍላጎት አላት አሉ።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ አጠቃላይ የለውጥ ስራዎች በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
አምባሳደሩ በፓኪስታን ለነበራቸው የስራ ቆይታ ለፓኪስታን ህዝብና መንግስት ምስጋና አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በመመረቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ፤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ አድንቀዋል።
የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ ደረጃ ለማድረስ መንግስታቸው ፍላጎት እንዳለው ገልጸው፤ በአፍሪካ በሚደረገው የጉብኝት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ቅድሚያ ላይ እንደሆነች ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በፓኪስታን በማስተዋወቅ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፓኪስታን የቀጥታ በረራ እንዲጀምር በማስቻል አምባሳደር ጀማል ጠንካራ መሰረት መጣላቸውን አንስተዋል።
አምባሳደሩ በፓኪስታን በነበራቸው የስራ ጊዜ ውጤታማ ተግባር ማከናወናቸውን መግለጻቸውን በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!