Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ስዊድን ትብብራቸውን ለማጠናከር መከሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከስዊድን ፍትሕ ሚኒስትር ዴዔታ አንደርሽ ሆል ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት÷ ኢትዮጵያ እና ስዊድን ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

በፍትሕ ዘርፍ እየተካሄደ ያለው ትብብር እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች የሀገራቱን ግንኙነት ይብልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.