የኢትዮጵያና የኖርዌይ የልብ ሕክምና አጋርነት ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የመኖር ተስፋ ሰጥቷል – ፕሬዚዳንት ታዬ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና የኖርዌይ የልብ ሕክምና አጋርነት ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የመኖር ተስፋ ሰጥቷል አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡
የኢትዮ-ኖርዌይ የልብ ሕክምና የአቅም ግንባታ እና የሕይወት አድን የ10 ዓመታት አጋርነት ጉዞ ላይ ያተኮረ ሲምፖዚየም ተካሂዷል።
ፕሬዚዳንት ታዬ በወቅቱ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ በጤናው ዘርፍ በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ።
የዚህ ትብብር አካል የሆነው የኢትዮጵያ እና የኖርዌይ የልብ ሕክምና አጋርነት በጤናው ዘርፍ ያበረከተውን አስተዋፅኦ አድንቀዋል፡፡
ተቋሙ በኢትዮጵያ በርካታ የነፍስ አድን ስራዎችን በማከናወን ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የመኖር ተስፋን ሰጥቷል ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ ተቋሙ ላከናወነው በጎ ተግባር መንግሥት ዕውቅና ይሰጣል ብለዋል፡፡
በሲምፖዚየሙ በኖርዌይ መንግሥት እና በኦስሎ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ድጋፍ በርካታ ኢትዮጵያውያን የልብ ሕክምና ስፔሻሊስቶች፣ የቀዶ ጥገና ባለሙያዎች እና ነርሶች ከፍተኛ ሥልጠና ማግኘታቸው ተገልጿል።
ይህም ኢትዮጵያ በዘርፉ የነበረባትን የባለሙያ እጥረት ለመቅረፍ ትልቅ እገዛ ማድረጉ ተነሥቷል።