ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጊምቢ ከተማ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታን አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ ‘ቢፍቱ ጊምቢ’ 2ኛ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል፡፡
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና ሌሎች የኦሮሚያ ክልል የሥራ ሃላፊዎች በምዕራብ ወለጋ ዞን የትምህርት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት በምስራቅ ወለጋ ዞን እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሥራዎችን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለትም በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ ‘ቢፍቱ ጊምቢ’ ሁለተኛ ደረጃ ሞዴል ት/ቤት ግንባታን ማስጀመራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡