የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ከዓለም አቀፉ የእሴት-ተኮር ባንኮች ትብብር ልዑክ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ከዓለም አቀፉ እሴት-ተኮር ባንኮች ትብብር ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ የህብረቱን እሴት-ተኮር የባንክና አካታች የፋይናንስ አገልግሎት አሰጣጥ ተሞክሮን መለዋወጥ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ሽግግር አስተዋኦ የሚያበረክቱ ዘላቂ የፋይናንስ ሞዴሎችን መለየት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡
በዚህም የህብረቱ ልዑካን እና የኢትዮጵያ ሀገር በቀል ባንኮች አመራሮች በኢትዮጵያ በዘርፉ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ እና በፋይናንስ ዘርፉ እየተደረጉ ስላሉ ማሻሻያዎች ዙሪያ መምከራቸውን የባንኩ መረጃ ያመላክታል።
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ÷ ባንኩ ስትራቴጂያዊ አጋርነቶችን ለማፍራት ሁሉን አቀፍ እና ለባለሃብቶች ተስማሚ የሆነ የባንክ ምህዳርን ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።