አርሰናል በበርንማውዝ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በሜዳው ኤሚሬትስ ስታዲየም በርንማውዝን ያስተናገደው አርሰናል 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
የበርንማውዝን የማሸነፊያ ግቦች ዲያን ሁጅሰንና ኢቫኒልሰን ሲያስቆጥሩ አርሰናልን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ዲክላን ራይስ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ቀደም ብለው በተደረጉ ጨዋታዎች አስቶንቪላ ፉልሃምን 1 ለ 0 እንዲሁም ሌስተር ሲቲ ሳውዝሃምፕተንን 2 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡
በሌላ በኩል ኤቨርተን እና ኢፕስዊች ታውን ያረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡